Addis Capital
Addis Capital Goods Finance Business S.co
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ን.ስ አ.ማ
I
የኩባንያው ተልዕኮ
በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ እውቀት እና ክህሎት ኖሯቸው በጥቃቅን፣ አነስተኛና ታዳጊ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ወይም ለመደራጀት ፍላጎት ኖሯቸው በካፒታል ዕቃ እጥረት ምክንያት ስራቸውን መስራት ላልቻሉ እንዲሁም ስራቸውን ለማስፋት ለሚፈልጉ ኢንተርፕራዞች፣ ለግለሰቦች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች ቀጣይ እና አስተማማኝነት ያለው የካፒታል እቃ ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡
የኩባንያው ራዕይ
ዓላማ
በ2030 እ.ኤ.አ ቀጣይነቱ እና አስተማማኝነቱን ያረጋገጠ ታማኝ የካፒታል ዕቃዎች ፋይናንስ አቅራቢ ለመሆንና በምስራቅ አፍሪካ ሞዴል የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ መሆን ነው፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በአምራችነትና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ለኢንዱስትሪው ሰፊ መሰረት የሚጥሉ በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ እና ለሚሰማሩ የጥቃቅን አነስተኛና ታዳጊ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተመራቂዎች፣ ወጣት እና ሴት ሥራ ፈጣሪዎች እና ውጤታማ የንግድ ተቋማትን፣ ለግለሰብ እና ማህበራት፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች እና ሎችም የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ ነው::
.