Addis Capital

          (  0111262411 / 0111263514           * 54782 Fax : 0111262445 Email : addiscapital@addiscapital.com.et                                                                  

 Addis Capital Goods Finance Business S.co

አዲስ  የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ን.ስ አ.ማ 

Select Language

                         .

                         .

    በኩባንያው የቅርብ ዜናዎች

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

 1.ኩባኒያው የ 2014 የግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ፤

3. ኩባንያው የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄደ

                   ቀን፡- 25/05/2014 ዓ.ም  

‘’ዘርፉ በአህጉርና በሀገር ደረጃ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀጣይ 6 ወራትም በአስተሳሰብና በአመለካከት አንድ ሆነን መስራት ይጠበቅብናል’’ በማለትም አክለዋል፡፡

በኩባኒያው የካፒታል ዕቃ ማስተላለፍ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታቸው መኩሪያ በበኩላቸው የኩባኒያው ሰራተኞች በአሰራር ሂደቱ ላይ ግንዛቤቸው ይበልጥ ይሰፋ ዘንድ  የኦፕሬሽናል ፖሊሲን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ በማድረግ በምላሹም ገንቢ ውይይት የተደረገ ሲሆን በበጀት ኣመቱ የግማሽ ዓመት ሪፖርት አፈጻጸምን አስመልክቶ እንዲሁ የፕላኒንግ፣ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ መለስ በላይ አቅርበው የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው በሚመለከታቸው የኩባኒያው የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

 

 

 

ኩባኒያው በግማሽ ዓመት ውስጥ ለ202 ኢንተርፕራይዞች በብር 117,789,022.79 የሚያወጡ 1,066 የተለያዩ ለማምረቻና አገልግሎት የሚዉሉ ካፒታል ዕቃዎችን መስጠት  ተችሏል፡፡

በእለቱ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኩባኒው ማኔጂንግ ዳይሬክተር  አቶ መሳይ እንሴኔ  “የኩባኒያው ተልዕኮ ከፍተኛ  ተፈላጊና ፣አዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንደመሆኑና  የሰው ህይወት የሚቀይርም ጭምር  በመሆኑ በምን መልኩ አገልግሎት እየሰጠን ነው ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን” በማለት የገለፁ ሲሆን፡፡

 

ኩባኒያው ለ129 ደንበኞች 167,387,953.88 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 743 የተለያዩ የካፒታል ዕቃዎች በግዥ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ2014 በጀት ዓመት 6 ወራት አፈጻጸም የተሻለ መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡

አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሰራ አ.ማ. ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ አጋርነታቸውን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ቸርችል ጎዳና በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የደም ልገሳ መርኃ ግብር አካሂደዋል፡፡

የደም ልገሳ መርኃ ግብሩን  ለማስጀመር  በስረፍራው ሲያስተባብሩ ያገኘናቸው የኩባኒያው ማኔጂንግ ዳይራክተር የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ የደም – ልገሳ መርኃ ግብሩን አስመልክቶ “በዕለቱ የተደረገው የደም ልገሳ መርኃ ግብር መከላከያ ሰራዊቱ ሀገርን ለማዳን እያደረገ ያለውን የህይወት መስዋዕትነትን አስመልክቶ የኩባኒያውም ሰራተኞችም ደም በመለገስ ደጀንነታቸውን የሚገልጹበት ሀገር ለማዳን ከሚደረጉ ተግባራት መካከል  አንዱ አካል ነው”ብለዋል፡፡

 

በተጨማሪም  እንደ ሀገር ወደ ጦርነት ተፈልጎ የተገባ  ሳይሆን ተገደን ሀገርን ለማዳን የተገባበት በመሆኑ የኩባኒያው ሰራተኞችም ሆኑ የስራ ኃላፊዎች ደም ከመለገስ ጎን ለጎን  ሁሉም በሚገኙበት የስራ  መስክ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

ከተራቁጥር 2 የቀጠለ

በኩባኒያው የአስተዳደር ዘርፍ ም/ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተገኝ ጦፋ በበኩላቸው  መርኃ ግብሩን አስመልክተው እንደገለጹት ሀገራችን አሁን ላይ ያለችበት ሁኔታ እያንዳንዱ ዜጋ በሚችለው መስክ አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ሁሉ የኩባኒያውም ሰራተኞች ደማቸውን በመለገስ የማይተካ ህይወቱን መስዋዕት በማድረግ ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊታችን ደም መለገስ የደጀንነት መገለጫ  ሌላኛው መንገድ ነው፡፡እንደ ሀገር ወደ ጦርነት ተፈልጎ የተገባ  ሳይሆን ተገደን ሀገርን ለማዳን የተገባበት በመሆኑ የኩባኒያው ሰራተኞችም ሆኑ የስራ ኃላፊዎች ደም ከመለገስ ጎን ለጎን  ሁሉም በሚሉት መስክ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

በተጨማሪም  በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መሪነት በሀገር አቀፍ ደረጃ በመከናወን ላይ የሚገኘው የአረንጓዴ ልማት አሻራን ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዊችን ከማስገኘት አኳያም ጠቀሜታው የላቀ ነው በማለት አክለዋል፡፡

በኩባኒያው አስተዳደር ዘርፍ ም/ማኔጂንግ የሆኑት አቶ ተገኝ ጦፉ በበኩላቸው ኩባኒያው ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በቀጣይ በኃላፊነት ውኃ የማጠጣትና የመንከባከብ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ከ1መቶ 3 በላይ የተቋሙ ሰራተኞች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ከ4መቶ በላይ ችግኖችን ከ10ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ እና መንግስት ሊያወጣ የሚችለው ከ30ሺ ብር በላይ ገንዘብ ማዳን መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

ኩባንያው በባለፉት አመታትም እንዲሁ የአረንጓዴ ልማት መርኃ ግብር ከማሳካት አንጻር አሻራ ማሳፉ ይታወሳል፡፡ በቀጣይም የደም ልገሳ መርሃ ግብር ለማካሄድ ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

የአዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ አመራሮች እና ሰራተኞች የአረንጓዴ ልማት መርኃ ግብር የተሳካ እንዲሆን በተለምዶ ሰይጣን ቤት ተብሎ ከሚጣርው አካባቢ የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡

የችግኝ ተካላውን አስመልክተው የካባንያው ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ እንደገለፁት ከሆነ የታላቁ ህዳሴ ግበድብ የ2ኛ ዙር ውኃ ሙሌት ድል በተበሰረበት አጋጣሚም ኩባኒያችን የችግኝ ተከላ መርኃ-ግብርን በተሳካ ሁኔታ ማካኔድ መቻሉ መጪው ጊዜ በከተማችንም ሆነ በአሁገራችን የሰላምና ብልፅግና መስፈን የብሩህ ገፅታ ነጸብራቅ ተምሳሌት ነው፡፡ ብለዋል

 

‘’ደም በመለገስ ሂደት ለ 21 ጊዜ ተሳትፌአለሁ’’ በማለት ሀሳቡን የገለፀው  በአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መለስተኛ ሊዝ ኦፎሰር ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘው ወጣት ይታይልኝ መዝገቡ ደም በመለገስ የብዙዎችን ህይወት ማዳን እንደሚቻልና በሁሉም ዜጋ ሊለመድ የሚገባው ከመሆኑ ባለፈ  ጤንነትም ጭምር መሆኑን ገልጽዋል፡፡

በስፍራው ተገኝተው የደም ልገሳ ሂደቱን ሲያስተባብሩ ያገኘናቸው  ከብሔራዊ ደም ባንክ ማዕከል የመጡት ባለሙያ አቶ ኢያሱ ኤርጌቾ እንደነገሩን ከሆነ ደም በዋጋ የማይተመንና ራስን አሳልፎ እንደመስጠት የሚቆጠር ልገሳ በመሆኑ የኩባኒያው ሰራተኞች እያደረጉት የሚገኘው የደም ልገሳ አድናቆት የሚቸረውና ለሌሎችም በአርኣያነት የሚወሰድ  ነው፡፡

ከእያንዳንዳቸው የኩባኒያው ሰራተኞች  350 ሚ.ሊ የደም ልገሳ የተደረገ ሲሆን ይህም ሲሰላ  ከ22 ዩኒት በላይ መሆኑንና በትንሹ የ22 ሰዎችን ህይወት መታደግ እንደሚቻልም አቶ ኢያሱ አክለዋል፡፡

 

‘’ለመከላከያ አጋርነቴን ማሳየት የምችለው ነገ የሚተካውን ደሜን ዛሬ በለመለገስ ህይታቸውን በማትረፍ ነው’’ ያሉት በኩባኒያው ከፍተኛ የሊዝ ኦፊሰር የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ሺፈራው በቀጣይም በሚዘጋጁ መሰል መርኃ ግብሮች ተሳታፊ እንደሚሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ያነጋገርናቸው አንዳንድ የኩባኒያው ሰራተኞች እንደተናገሩት በየ 3 ወራት በቋሚነት ደም ለመለገስ መነሳሳታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ኩባኒያው የደም ልገሳውን መርኃ ግብሩን ከማስኬድ ባለፈ በተለያዩ ጊዜያት ሰራተኞችን በማስተባበር ለመከላከያ ሰራዊታችን የአንድ ወር ደመወዛቸውን በአንድ ዓመት  ከፍለው ለማጠናቀቅ ቃል በገቡት መሰረት ከደመወዛቸው እየተቆረጠ ሲሆን ለ2ኛ ዙርም በተመሳሳይ ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን በ አንድ ዓመት ከፍለው ለማጠናቀቅ  ቃል መግባታቸው ይታወቃል፡፡   

ኩባኒያም ለመከላከያ ሰራዊቱ እገዛ ከ10ሚሊየን ብር በላይ መለገሱንም ማወቅ ተችሏል፡፡

2. የኩባኒያው ሰራተኞችና የስራ        ኃላፊዎች የደም – ልገሳ አደረጉ